በሠመራ ዩኒቨርስቲ የሜጋ ስኬል ሪሰርች ፕሮፖዛል ግምገማ Work Shop ተካሄደ።

በሠመራ ዩኒቨርስቲ የምርምር እና ፐብሊኬሽን   ዳሬክቶሬት አዘጋጅነት በተቋማችን ለመጀመሪያ ጊዜ የMega -Scale Research proposals Review Work Shop ዛሬ ረቡዕ 5/5/2013ዓ/ም አካሂዳል። በወርክሾፑ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግራቸውን ያደረጉት የዩኒቨርስቲው የም/ማ/አ/ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ቤተልሄም ዳኛቸው ፣ ምርምር ሁሌም  አድስ ነገር መፍጠር ነው ፣ምርምር  ዘላቂ ልማት ለመፋጠር ጉልህ ሚና አለው ብለዋል።ከዚህም አንዱ ትልልቅ የምርምር ዕድሎችን መፍጠር ነው ብለዋል።   የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዱረህማን በበኩላቸው ዩኒቨርስቲያችን የሜጋ ፕሮጀክት ምርምር ለመጀመሪያ ጊዜ ለመሰራት መጀመሩን በይፋ አበስረዋል። ከዚሁም ጋር አያይዘው በዚህ የምርምር ፕሮፖዛል ግምገማ ላይ የተሳተፉ ትልልቅ ባለሙያዎች ፣ፕሮፌሰሮች ፣መምህራን እና ሌሎች አጋር አካላቶች መልካም ጅማሮ እንድሆንላቸው ምኞታቸውን ገልፀዋል። ይህ የሜጋ ስኬል ምርምር በውስጡ  3 ፕሮፖዛል አካታል።እነሱም ፣
1,intergrating Afar cultural studies for social transformation and sustainable Development.  2,Geo-tourism Destination: as implication to Geo-park Development in Afar Regional State.      3,Flood and Drought Risk management  and its mitigation Strategies.
የሚሉ ሲሆኑ ለክልሉ እና ለማህበረሰቡ እድገት ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተገልፃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *